ጙሹር
ጙሹር (ወይም ጚሹር) በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ የኪሽ ከተማ መጀመርያው ንጉሥ ነበረ። በዚሁ ጥንታዊ ሰነድ መሠረት፣ ከማየ አይህ ቀጥሎ ኪሽ መጀመርያ የተነሣ መንግሥት እንደ ነበር ይላል። ጙሹርም ለ1200 አመታት በሱመር እንደ ነገሠ ይላል።
የኪሽ 1ኛ ሥርወ መንግሥት መስራች ጙሹር መታወቂያ ወይም ኅልውና የሚያስረዳ ቅርስ ገና አልተገኘም። ታሪካዊ ከሆነ ግን ምናልባት በ2450 ዓክልበ. ግድም ኖሯል።
Text is available under the CC BY-SA 4.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.