For faster navigation, this Iframe is preloading the Wikiwand page for ኮንታ.

ኮንታ

የኮንታ ብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ኮንቲኛ ሲሆን፣ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ከንግግር ቋንቋነት ባሻገር የትምህርትና የሥራ ቋንቋ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ዳውሮኛጋሞኛወላይትኛአማርኛ ይናገራሉ።

የኮንታ ብሔረሰብ በዋናነነት በኮንታ ልዩ ወረዳ በሚገኙ በገጠር እና የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን፣የተወሰኑ የብሔረሰቡ አባላት በተለያየ የሥራ መስክ ተሰማርተው በአጎራባች አካባቢዎች እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የኮንታ ብሔረሰብ የሚገኝበት አካባቢ ሜዳማ፣ ተራራማና ሸለቆ የሆነ መልክአ ምድራዊ ገጽታ ሲኖረው የብሔረሰቡ የኢኮኖሚ መሠረት የሆነው እርሻና ከብት እርባታ ሲሆን፣ የተወሰነው የኀብረተሰብ ክፍል የተለያዩ የዕደ ጥበብ ምርቶች በማካሄድና በማምረት የዕለት ተዕለት ሕይወቱን ይመራል፡፡እንደ 1999 ህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ የኮንታ ህዝብ ብዛት 117,000 በላይ መሆኑን የምጦቅም ብሆንም በተጨባጭ የወረዳው ህዝብ!! ብዛት ከ250,000-300,000 እንደ ማይተናነስ አሁን ከለው የህዝብ አሰፋፈር ሳምፕል ቆጠራ መረዳት ይቻላል ። በወቅቱ ካለው የመሠረቴ ልማት እጥረትና ከመሬት ወጣ ገብነት ጋር ተያይዞ የ1999 መረጃ የተዛባና የአከባቢው የህዝብ ቁጥር መረጃ የማይገልፅ ነው ። በመሆኑም በወረዳው በአሁኑ ሰዓት ያለው ህዝብ ቁጥር ከለላ አከባቢ መተው ከሰፈር ሰፋሪዎች ጋር ከ300,000 በላይ ይገመታል ።

የኮንታ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር መዋቅር ተዋረዳዊ ኃላፊነትና ተግባር ባላቸው የተለያዩ ክፍሎች የተደራጀ ነው፡፡ በእዚህ መዋቅር የሁሉም የበላይ ካዎ ወይም ንጉስ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከማላ ጎሳ ይመረጣል፡፡ በኮንታ ብሔረሰብ ስድስት ባህላዊ የጋብቻ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህም በቤተሰብ ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ቦሣ) የለፋ ጋብቻ (ላታ) በተጋቢዎች ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ማቆ) የቃል ጋብቻ (ያኤኤኩዎ) እና ሚሽቶ (የምትክ ጋብቻ) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህ የጋብቻ ዓይነቶች በብዛት ሲከናወን የሚስተዋለው በቤተሰብ ስምምነት የሚፈጸመው የቦሣ ጋብቻ ነው፡፡

ከብሔረሰቡ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ፂፄ፣ ጫቻ፣ ዛይ፣ዲንኬ እና ኡልዱዶ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የትንፋሽና የምት የሙዚቃ መሣሪያዎች ለለቅሶና ለደስታ ጊዜ ያገለግላሉ፡፡ በተለይ ኡላዱዶ የተሰኘው የትንፋሽ መሣሪያ ከድኩላ ቀንድ ተበስቶ የሚሠራ ሲሆን ከብቶቻቸው ሆራ (ጨውነት ያለው ውሃ) ሊያጠጡ የሚወስዱ እረኞች ይነፉታል፡፡

የኮንታ ባህላዊ የቤት አሠራር ከፍልጥ እንጨት፣ ከቀርከሀ ከሰንበሌጥና ከሣር የሚዘጋጅ ሲሆን በደጋውና በቆላው አካባቢ ልዩነት አለው፡፡

ሱልሶ፣ ሲሊሶ፣ ኡስታ፣ ጨዲያ፣ ኩበዋ፣ ቦሩዋ (ዱቢያ) እና ባጨራ የኮንታ ብሔረሰብ ዋነኛ ባህላዊ ምግቦች ናቸው፡፡ ሲልሶ ለአብነት ከምን እንደሚሠራ እንይ፡፡ ሲልሶ ከጥሬ ሥጋ፣ ከቅቤ፣ ከደም፣ ከሀሞት እና ከተለያዩ የማጣፈጫ ቅመሞች ከተዘጋጀ በኋላ ከተለበለበና በክብ በተቆረጠ የእንሰት ቅጠል ላይ ለቤተሰቡ አባላት ይቀርብና በቡላ ወይም በቆጮ ይበላል፡፡

በብሔረሰቡ ወንዶች ከአቡጀዲ በእጅ የተሰፋ እጀ ጠባብ ሸሚዝና ሱሪ እንዲሁም ሀሲያ የተባለ በእጅ የተፈተለ ልብስ ሲለብሱ ሴቶች በኋላ በኩል ባለወጥ ጥለት የሆነውን ማዳ የተባለ የእጅ ፈትል ይለብሳሉ፡፡

wende konta ወንዴ ኮንታ

ኮንታ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።

{{bottomLinkPreText}} {{bottomLinkText}}
ኮንታ
Listen to this article

This browser is not supported by Wikiwand :(
Wikiwand requires a browser with modern capabilities in order to provide you with the best reading experience.
Please download and use one of the following browsers:

This article was just edited, click to reload
This article has been deleted on Wikipedia (Why?)

Back to homepage

Please click Add in the dialog above
Please click Allow in the top-left corner,
then click Install Now in the dialog
Please click Open in the download dialog,
then click Install
Please click the "Downloads" icon in the Safari toolbar, open the first download in the list,
then click Install
{{::$root.activation.text}}

Install Wikiwand

Install on Chrome Install on Firefox
Don't forget to rate us

Tell your friends about Wikiwand!

Gmail Facebook Twitter Link

Enjoying Wikiwand?

Tell your friends and spread the love:
Share on Gmail Share on Facebook Share on Twitter Share on Buffer

Our magic isn't perfect

You can help our automatic cover photo selection by reporting an unsuitable photo.

This photo is visually disturbing This photo is not a good choice

Thank you for helping!


Your input will affect cover photo selection, along with input from other users.

X

Get ready for Wikiwand 2.0 🎉! the new version arrives on September 1st! Don't want to wait?