ኪንሻሳ
ኪንሻሳ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1998 ዓ.ም.) 8.9 ሚሊዮን ሆኖ ይገመታል። ከተማው 04°18′ ደቡብ ኬክሮስ እና 15°18′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ኪንሻሳ በ1873 ዓ.ም. በጀብደኛው ሄንሪ ሞርቶን ስታንሊ ተመሠርቶ ስሙ ለቤልጅግ ንጉሥ 2 ሌዮፖልድ ክብር ለዮፖልድቪል ሆነ። በ1912 ዓ.ም. የቤልጅግ ቅኝ አገር መቀመጫ ወደዚያ ከቦማ ተዛወረ። በድሮው ዘመን የአሣ አጥማጅ መንደር በዚያ 'ኪንሻሳ' ስለተባለ፣ በ1958 ዓ.ም. ስሙ እንደገና ኪንሻሳ ሆነ።
Text is available under the CC BY-SA 4.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.