ቅንጭብ
ቅንጭብ ወይም እጸ ነበልባል (Kleinia) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ወገን ነው።
ከዚህ ወገን ውጭ የሆነ ሌላ ዝርያ (Euphorbia tirucalli) ደግሞ «ቅንጭብ» ተብሏል።
የቅንጭብ ዝርያዎች በሰፊ በተለይም በወይና ደጋ ይገኛሉ።
ቅንጭብ ለሰውም ሆነ ለከብት ምንም ጥቅም ስለሌለው በተፈጀ መሬት ላይ ይተርፋል።
ሌላ አይነት ማገዶ ባይገኝም ዕንጨቱ ቢጠቀም ኖሮ፣ ጢሱ ለዓይን እጅግ አስቸጋሪ ነውና ጉዳት ያደርጋል። ስለዚህ ለማገዶ እንኳ አይስማማም።[1]
- ^ አማራ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
Text is available under the CC BY-SA 4.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.