For faster navigation, this Iframe is preloading the Wikiwand page for ቅኔ.

ቅኔ

ማለት፡ 'ቀነየ' ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ አመሰገነ (ምስጋና) ማለት ነው። ወይም፡ 'ቀነየ' ፡ገዛ፡ የሚለውን፡ አንቀጽ፡ ያስገኘ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ፍችውም፡ 'መገዛት'፡ ማለት፡ ነው። 'ቁሙ፡ እንከ፡ ወኢትሑሩ፡ ዳግመ፡ ውስተ፡ አርዑተ፡ ቅኔ'፡ እንዲል፡ (ገላ.፥5፥1)፥ ቅኔ፡ ማለት፡ መገዛት፡ ማለት፡ ከኾነ፥ ይህ፡ ከያንዳንዱ፡ ሰው፡ በየጊዜው፡ የሚመነጨው፡ እንግዳ፡ ድርሰት፡ ስለ፡ ምን፡ ቅኔ፡ ተባለ፡ ቢሉ፥ ፍጡር፡ ዐዲስ፡ ዐዲስ፡ ምስጋና፡ እየደረሰ፡ በማቅረብ፥ ለፈጣሪው፡ መገዛቱን፡ የሚገልጥበት፡ ስለ፡ ኾነ፡ ነው። ለፍጡራን፡ የሚደረሰውም፡ ቅኔ፥ ቅኔው፡ የሚደረስለት፡ ፍጡር፡ ከቅኔ፡ ደራሲው፡ በላይ፡ ክብር፡ ያለው፡ መኾኑን፡ የሚገልጽ ፡ ድርሰት፡ ስለ፡ ኾነ፥ መገዛትን፡ ከማመልከት፡ የራቀ፡ አይደለም።

አንድም፥ ሕዋሳተ፡ አፍኣን፣ ሕዋሳተ፡ ውስጥን፡ ለኅሊና፡ አስገዝቶ፥ በተወሰነ፡ ቍርጥ፡ ሐሳብ ፡ የሚታሰብ፡ ስለ፡ ኾነ፥ ቅኔ፡ ተብሏል። ይኸውም፡ ሊታወቅ፥ በቅኔ፡ ምስጢር፡ ልቡ፡ የተነካ፡ ሰው፥ ቅኔ፡ በሚያስብበት፡ ጊዜ፥ እፊቱ፡ የሚደረገውን፡ ነገር፡ እያየ፣ እየሰማ፥ አይሰማም። ከዚህም፡ የተነሣ፥ በጎንደሮች፡ መንግሥት፥ የቍስቋሙ፡ አለቃ፡ በእልፍኙ፡ ውስጥ፡ ምንጣፉን፡ አስነጥፎ፥ መጻሕፍቱን፡ እፊቱ፡ ደርድሮ፥ ለበዓለ፡ ቍስቋም፡ የሚቀኘውን፡ ቅኔ፡ ሲያወጣና፡ ሲያወርድ፥ ንጉሡ፡ ዘው፡ ብለው፡ ቢገቡ፥ ልቡ፡ ተመሥጦ፥ ሊያያቸው፡ ባለመቻሉ፥ ቀና፡ ብሎ፡ ሳያያቸው ፡ ቁጭ፡ እንዳለ፡ ቀረ። ንጉሡም፥ ነገሩ፡ ደንቋቸው፥ ፍጻሜውን፡ ለማየት፥ ርሱን፡ ዐልፈው፡ ዐልጋ፡ ላይ፡ ተቀምጠው፥ ኹኔታውን፡ ይመለከቱ፡ ዠመር።

ብዙ፡ ሰዓት፡ ካሳለፈ፡ በዃላ፥ አእምሮው፡ ሲመለስ፥ ንጉሡ፡ ተቀምጠው፡ ቢያይ፥ ደንግጦ፡ ተነሥቶ፡ እጅ፡ ነሣ። ንጉሡም፦ ምነው፧ ምን፡ ኾነኽ፡ነው፧ ቢሉት፦ ጃንሆይ፥ ቍስቋምን፡ ያኽል፡ ደብር ፡ አምነው፡ ሾመውኛል፤ ለበዓል፡ የተሰበሰበው፡ ሰው፡ አለቃው፡ ምን፡ ይናገር፡ ይኾን፧ እያለ፡ ዐይን፡ ዐይኔን፡ ሲያየኝ፥ ያልኾነ፡ ነገር፡ ቢሰማ፡ ደብሩን፡ አዋርዳለኹ፥ ጃንሆይንም፡ አሳማለኹ፥ እኔም፡ አፍራለኹ፡ ብዬ፥ ቅኔ፡ እቈጥር፡ ነበር፡ አለ፡ ይባላል።

አንድም፥ ቅኔ፡ ማለት፥ 'ተቀንየ'፡ ሙሾ፡ አወጣ፥ ግጥም፡ ገጠመ፥ አራቆ፡ ተናገረ፥ አዜመ፥ አንጐራጐረ፥ መራ፥ ዘፈነ፡ ካለው፡ የወጣ፡ ጥሬ፡ ዘር፡ ነው። ስለዚህ፥ ቅኔ፡ ማለት፥ ባጪሩ፥ ጠቅላላ፡ ትርጕሙ፥ ሰው፡ ከራሱ፡ አንቅቶ፡ ለእግዚአብሔር፡ ዐዲስ፡ ምስጋና፡ ላቅርብ፡ ባለ፡ ጊዜ፥ ምሳሌ መስሎ፥ ምስጢር፡ አሻሽሎ፡ ግጥም፡ በመግጠም፥ የልቦናውን፡ ዕውቀት፣ የአእምሮውን፡ ርቀት፡ የሚገልጽበት፥ የዕውቀቱን፡ ደረጃ፡ የሚያስታውቅበት፥ የሰሚንም፡ ልቡና፡ የሚያነቃቃበትና፡ የሚያራቅቅበት፡ ድርሰት፡ ማለት፡ ነው። ከዚህም፡ የተነሣ፥ መጋቢ፡ መርሻ፡ ኀይሉ፡ የተባሉ ፡ የዲማው፡ ባለ፡ ቅኔ፦ የሰውን፡ ዕውቀቱን፡ መጠን፡ የማውቀው፡ በቅኔው፡ ነው፡ ይሉ፡ ነበር፡ ይባላል።

ከስም ውስጥ ይተሽሞነምነ ወርቅ እንደሚወጣ ሁሉ ከቃላትም የተደበቀ ምስጢር ሲወጣ ያ ጥበብ ሰምና ወርቅ (ቅኔ) ይሰኛል።

የአማርኛ ቅኔወች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የግዕዝ ቅኔወች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ንሁር በፍናዌሀሙ ወንትሉ በኣሰሮሙ

ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ!

ህፃናት አእባን ኢትሁሩ ከዊነ እክሙ ሠላሳ ዉስተ ቤተ ዮሤፍ ባእድ አምጣነ ሀሎ አንበሣ

ኒቆዲሞስ ገብር በሌሊተ ግርማ ቀጥቅጦ ለአስተብርኮ ብርክ ጸርከ እስከ ይወጽዕዘሂጦ

{{bottomLinkPreText}} {{bottomLinkText}}
ቅኔ
Listen to this article

This browser is not supported by Wikiwand :(
Wikiwand requires a browser with modern capabilities in order to provide you with the best reading experience.
Please download and use one of the following browsers:

This article was just edited, click to reload
This article has been deleted on Wikipedia (Why?)

Back to homepage

Please click Add in the dialog above
Please click Allow in the top-left corner,
then click Install Now in the dialog
Please click Open in the download dialog,
then click Install
Please click the "Downloads" icon in the Safari toolbar, open the first download in the list,
then click Install
{{::$root.activation.text}}

Install Wikiwand

Install on Chrome Install on Firefox
Don't forget to rate us

Tell your friends about Wikiwand!

Gmail Facebook Twitter Link

Enjoying Wikiwand?

Tell your friends and spread the love:
Share on Gmail Share on Facebook Share on Twitter Share on Buffer

Our magic isn't perfect

You can help our automatic cover photo selection by reporting an unsuitable photo.

This photo is visually disturbing This photo is not a good choice

Thank you for helping!


Your input will affect cover photo selection, along with input from other users.

X

Get ready for Wikiwand 2.0 🎉! the new version arrives on September 1st! Don't want to wait?